ጥቅምት 4፣ 2017 ዓ.ም 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር እና ተጠሪ ተቋም በጋራ ተከብሮ ዋለ ፡፡
ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
እለቱን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልክታቸውም በዓሉን ስናከብር ለዚህ ሰንደቅ ዓላማ ክብር ለሃገር አንድነት ሉዓላዊነትና ክብር የሚከፈለውን መስዋትነት ለአንድነታችንና አብሮነታችን የጋራ አርማ መሆኑን በማስታወስ ድህነትን እና ኋላቀርነትን አስወግደን ኢትዮጵያን በልማት በድሞክራሲ ጎዳና ውስጥ በልጽጋ የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡
